
Ethiopian Records
Endeguena Mulu, aka Ethiopian Records, is one of the leading lights in Ethiopia’s burgeoning electronic music scene. Sometimes using nothing more than a computer, Ableton software, and a Push controller, he makes music inspired by traditional music from all over the country and the continent. He experiments with traditional rhythms and sonic palettes using electronic music-making tools to explore a future that is eternally Ethiopian and African. He calls what he does “Ethiopiyawi Electronic”.
He is an Electronic Azmari that has been carving sonic soundscapes for the past 14 years. One of the main pillars of the genre is Pan-Africanism. Ethiopian Records is also part of an electronic azmari band called Azmari Synthesis. An extension of his Ethiopiyawi Electronic concept, the band features five electronic instruments, four traditional instruments, and Ethiopian Records’ compositions, productions, and machines.
Ethiopian Records is also the co-founder of WAG Entertainment, a boutique specializing in holistic talent management, events, creative production, and corporate brand integration. WAG intends to fill the gap in representation, organization, and management for up-and-coming and established young professional musicians and artists who are shaping the future of Africa’s sound.
Releases
Qen Sew (1432R),
Letu Sinega (1432R)
Be Enqelf Lebe (1432R)
Ye Feqer Edaye (Arcola)
Taxi Sampler 01 – Rhythms & Vibes From The Spirit Of Young Africa (Crudo Volta)
የኢትዮጵያ ልጅ
የኢትዮጵያን ሪከርድሱ እንደገና ሙሉ በማበብ ላይ ለሚገኘው ኤሌክቶሮኒክ ሙዚቃ ብርሃን ይዘው ከመጡ የሙዚቃ ሰዎች አንዱ ነው። አንዳንዴ ኮምፒወተር ላይ አቤቶን የተባለ ሶፍትዌር እና ፑሽበተን በመጠቀም ብቻ በሀገሩ ባህል እና ትውፊት ላይ ያተኮሩ ሙዚቃዎችን ይሰራል። ኢትዮጵያው እና አፍሪካዊ ነገን ለመዳሰስ ፤ በባህላዊ ምቶች እና ባህላዊ የድምፅ መሳሪያዎች ላይ የኤሌክትሮኒክ ሙዚቃ መሳሪያዎችን ተጠቅሞ ሙከራዎችን ያደርጋል። ስራውንም ኢትዮጵያዊ ኤሌክቶሮኒክ ሲል ሰይሞታል። ኤሌክትሮኒክ አዝማሪ ነው።
ላለፉት 4 አመታት ልዪ የድምፅ አወጣጥን ሲፈልግ ኑሯል።
ኢትዮጵያዊ ኤሊክትሮኒክ ከአፍሪካዊ ባህል እና ሙዚቃ ጋር በጥልቅ የተቆራኘ እና የኤሌክትሮኒክ የሙዚቃ መሳሪዎችን
እና ቴክኖሎጂን የሚጠቀም የሙዚቃ አይነት ነው። ፓን አፍሪካኒዝም ከሙዚቃው አይነት ምሶሶዎች አንዱ ነው።
ኢትዮጵያዊ ኤሌክትሮኒክስ አዝማሪ የሚባል የኢትዮጵያዊ እኤክትሮኒክስ አዝማሪ ባንድ አለው። የኢትዮጵያዊ ኤሌክቶሪኒክስ ፅንሰ ሃሳብ ቅጥያ የሆነ፤አራት የባህል መሳሪያዎችን እና የኢትዮጵያን ሪከርድስን ቅንብር፣ፕሮዳክሽን እና መሳሪያዎች ይካተተ ባንድ ነው። ኢትዮጵያን ሪከርድ የዋግ ኢንተርቴመንትም አብሮ መስራች ነው። ጥራት ባለው ችሎታ ላይ ትኩረቱን ያደርገ የውክልና፣የዝግጅቶች፣የፈጠራ ፕሮዳክሽን እናም የኮረፐሬት ብራንድ ኢንተግሬሽን ድርጅት ነው። ዋግ ለጀማሬም ሆነ አንጋፋ ሙዚቀኞች በውክልና፣መድራጀት እና ማኔጅመንት ዙሪያ ያለውን ክፍተት የመሙላት አላማን ይዟል።

HOW DO YOU DEFINE ETHIOPIYAWI ELECTRONIC?
Ethiopiyawi Electronic for me is not a genre, it is a name I gave to what I do because I have to. Otherwise, people (especially in the western world) will give it the name and definition they want. Making music for me and especially the process of experimenting with music, exploring and experimenting with sounds from my country and continent, is a very personal process, it helps me define who I am to myself. Most importantly, it is a process of trying to find oneself that is constant and that should continue throughout someone’s life, and having it limited by walls like genre and inaccurate academic terms (terms like world music, ethnic music, tribal music, etc…) is destructive, which is why I decided to call what I do Ethiopyawi Electronic, and give myself the Ethiopian Records name. They are like working titles for me, we live in a world where some are appropriate from others, try to force their definitions and paradigms on others, gentrify spaces and ideas so me using these names is kind of a protection for my process.
It is not a genre, it’s a name for the process of what I do, trying to craft and express myself and what I encounter on this plane of existence and free my imagination. We have hundreds of cultures and ethnic groups in Ethiopia and thousands of them around our continent, and even more around the world, and the people who get to spearhead the connection of these cultures are very few in number. Each culture is a universe of its own, there are 7.7 billion people on this planet, each person is a universe of its own, a genre of its own and limiting oneself in genres for the ease of commodifying them is a crime, it is killing what is possible for what is convenient and unimaginative. So, I hope it continues to evolve in a way where it remains free and untethered.
ኢትዮጵያዊ ኤሌክቶሮኒክ
ኢትዮጵያዊ ኤሌክቶሮኒክ ለእኔ የሙዚቃ አይነት አይደለም። ስም መስጠት ስለኖረብኝ ነው የሰየምኩት። ካልሆነ ሰዎች ፤ በተለይም ምእራባውያኑ ፤ የራሳቸውን ስያሜ እና ትርጉም ሊሰጡት ይችላሉ። ሙዚቃ መስራት ፤ በሙዚቃ አዲስ ነገር መሞከር እንዲሁም የሃገሬን ድምፆች እና ባህሪ ላይ ሙከራ ማድረግ በጣም ውስጣዊ የሆነ እና የራሴ የምለው ነገር ነው። ማንነቴን ለራሴ ለማሳወቅ ይረዳኛል። ሰው ራሱን ለማግኘት በሚኖረ ጉዞ ላይ እድሜ ልኩን አጥር ሆነው የሚያግዱት አሻሚ ትምህርታዊ ቃላት (እንደ የአለም ሙዚቃ ፣ የብሄርሙዚቃ፣የጎሳ ሙዚቃ ወ.ዘ.ተ…) ጎታች ናቸው። ለዛም ነው የምሰራውን ሙዚቃ ኢትዮጵያዊ ኤሌክትሮኒክ ብዬ ለመጥራት እና ለስያሜም ኢትዮጵያን ሪከርድስ የሚል ስም ለመስጠት የወሰንኩት። እነሱ ለእኔ እንደ የስራ ስም ናቸው። የምኖርባት አለም ሌሎች ሊቀርፁን የሚሞክሩባት ፤ የራሳቸውን ትርጉም እና አስተሳሰ ሊጭኑብን የሚሹባት ከመሆኗ አንፃር እኔም እነዚህን ስሞች ለስራዬ ሂድት እንደ ጋሻ አድርጌ መርጫቸዋለው።
እንዳልኩት የሙዚቃ አይነት አይደለም፤ራሴን ለመግለፅ እንዲሁም አይምሮዬ ሳይገደብ የሚስለውን እና የህይወት ልምዴን ይገልፅልኛል የምለው ስም እንጂ። ኢትዮጵያ ውስጥ ከመቶ በላይ ብሄር ብሄረቦች ከሺ በላይ መገለጫዎችን ይዘው ይገኙባታል። አለም ስንል ደሞ ከዚህም እጅግ ይበዛል። የነዚህን ባህሎች ስብጥር እና ግንኙነት የሚያስተውሉት ግን ጥቂቶች ናቸው። እያንዳንዱ ባህል እንደየራሱ አለም ነው። 7.7 ቢሊዮን ህዝብ ባለባት አለም እያንዳንዱ ሰው በራሱ የራሱ ዘርፍ የራሱ አለም አለው። ስለሆነም ራስን በአንድ ሙዚቃ አይነት ገድቦ ለንግድ ማዋል ፈጠራን የሚገድል እና ምቾት የሚነሳ ስለሆነ ከወንጀል አይተናነስም። ስለዚህ ነፃ እና ያልታሰረ ሆኖ ማደጉን እንደሚቀጥል ተስፋ አደርጋለው።

WHAT IS THE DIFFERENCE BETWEEN DJS AND ELECTRONIC MUSIC?
A DJ itself has such a wide definition and there are so many ways of being a DJ and an electronic musician. I guess in our city’s night scene people view a DJ as someone who plays one song after the other, which is one very small possibility in the ways someone can be a DJ. The same goes for being an electronic musician. The categories are truly endless, which is why I am attracted to electronic music-making tools, they are still being defined, they are still being built and that gives room for people on our continent to leapfrog and take charge of our fate instead of just following what has already been set by westerners.
Technology, like everything, is a tool, and a tool is crafted in the image of its maker, for now how these tools are made is very limited to mostly just one kind of culture (even if that culture has built those tools by “borrowing” from cultures all around the world), these are mostly following one set of paradigms for making music and thinking, which is making money, being commercially viable, and viewing the world in the western capitalistic way. They are very limited imagination-wise and quite inaccessible to people. Like everything else, the definitions of a DJ and electronic music are for now very limited because they have yet to be radically redefined, reimagined, and reinvented by all of the cultures and people of the world.
ዴጄ ከኤሌክቶሪክ ሙዚቃ
ሁለቱም ከሚገናኙበት መንገድ አኳያ ለመመለስ የሚከብድ ጥያቄ ነው። ዲጄነትም ሆነ ኤሌክትሮኒክ ሙዚቀኛነት በራሱ ዘርፈ ብዙ ትርጉም ያለው ነው። የከተማችን ምሽት ክለቦች ገፅታን መነሻ በማድረግ በብዙዎች ዲጄዎች እንደ ሙዚቃ ቀያያሪ ብቻ ይታያሉ። ይህ ደግሞ አንድ ሰው ዲጄ ሊሆንበት ከሚችላቸው መልኮች ቅንጣቱ ነው። ማብቂያ የለሽ ዘርፎችን በውስጡ ይዟል። ለዛም ነው የኤልክትሮኒክ የሙዚቃ መሳሪያዎች ቀልቤን የሳቡት። ተሰርተው አላለቁም፤አሁንም እየተሻሻሉ ነው። እሱ ደግሞ እንደኛ ሙያው ውስጥ ላሉ ሰዎች ምእራብያውያኑ ነው ብለው ካስቀመጡት ውጭ የመሻሻል እድሉንም ሆነ የፈጥራ ነፃነትን እንዲኖረን ያደርጋል።
ቴክኖሎጂ እንደማንኛውም ነገር መሳሪያ ነው። መሳሪያ ደሞ የፈጣሪውን መልክ ይይዛል። ለዛም ነው(ምንም እንኳና ፈጣሪዎቹ በአለም ዙሪያ ካሉ ባህሎች “ቢበደሩም”) እነዚህ መሳሪያዎች የአንድ ባህል መልክ ብቻ የኖራቸው። እንዚህም አንድ አይነት ሙዚቃዊ አሰራር እና አስተሳሰብ ነው ያላቸው ፤ ገንዘብ መስራት እና በሙዚቃ ገብያ ውስጥ አዋጭ ሆኖ መገኘት። በአጠቃላይ አለምን በምእራባዊ ካፒታሊስት አይን ማየት። ወጣ ብሎ ለማሰብ ዝግ ከመሆናቸው አንፃር (ምንም እንኳን ከ30 አመት በፊት ከነበረው አንፃር ቢረክሱም፤ለቀሪው አለም እንደልብ ተደራሽ ባለመሆናቸው) የሚጠቀማቸውም ሰው በዛው ልክ ጥቂት ነው። እናም ልክ እንደሁሉ ነገር የዲጄ እና ኤሌክትሮኒክ ሙዚቃ ትርጉም የተገደበ ሊሆን ችሏል። ገና እንደአዲስ በሁሉም የአለማችን ባህሎች እና ህዝቦች መተርጎም፣መታሰብ እና መፈጠር ይኖርባቸውል።

WHAT ARE YOUR THOUGHTS ON THE ETHIOPIAN MUSIC INDUSTRY?
We don’t have an industry in Ethiopia, we have scenes. Untended, unsupported music scenes all over the country, from traditional music from every region to scenes in the capital like Ethio-Jazz and the contemporary pop scene. This means we haven’t yet fully been molded by the global world into a consumable, perishable amorphous blob, but it also means access to resources, access to airtime, access to studios, access to venues for traditional musicians, young musicians, experimental musicians, up-and-coming musicians, and musicians that don’t fit the Ethiopian mainstream is quasi-inexistent.
That is because access to these outlets is concentrated in the hands of very few people, and either intentionally or unintentionally, such gatekeepers limit what is possible. Such power is not meant to be concentrated in a few hands; it leads to conformity and mediocrity. This is dangerous because the lack of diversity of voices that could lead to the building of a local, authentic industry also means a lack of diverse voices and ideas in other sectors such as politics, academia, science, and agriculture. It is pretty much the same in the global mainstream too, it is also elite-based, but we can be more than the global mainstream, we could be a more healthy, inclusive, diverse, working-class, and majority-based cultural industry if that power was opened up to more people.
The other thing is the professional support (like lawyers, accountants, managers, PR, event bookings for musicians, artists, sound engineers, mastering, mixing, and acoustic engineers) is also almost non-existent, which makes things even worse for independent artists, forcing them to not be adventurous, bold. They self-censor and look for what can be sold, what has already been done, what’s trending in the country and around the world, instead of trying to forge their own path, they basically destroy who they are and what makes them unique and brilliant to fit into what they think makes money and what helps them achieve fame.
Having all the necessary professionals to support and build the music with you is very important because the process of putting out music, just like making a film or any other profession, requires different people with different expertise. I am not only collaborating with a manager; I co-created a talent boutique agency with my filmmaker friend and manager Leul Shoaferaw called WAG to create infrastructure not just for myself but also other artists.
ሙዚቃ በኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ ውስጥ የሙዚቃ ገፅታ እንጂ ኢንዱስትሪ የለንም። ከባህላዊ ሙዚቃዎቻችን ጀምሮ እስከ በመዲናችን ያሉት ኢትዮ ጃዝ እና ዘመነዊ ፖፕ ሙዚቃ ድረስ ቸል የተባለ እና ድጋፍ የተነፈገው የሙዚቃ ሁናቴ ነው ያለው። እሱ ማለት ደሞ ገና በሌላው አለም ግፊት ወደ ተገዥ ፤ የጠፋ እና ቅርፅ አልባ ማንነት አልተቀየርንም ማለት ነው። ቢሆንም ግን ለባህላዊ ፣ ወጣት ፣ ኤክስፐርመንታል እና በመምጣት ላይ ላሉ ሙዚቀኞች እንደ የአየር ሰዓት ፣ ስቱዲዮ እንዲሁም የማሳያ ቦታዎች የሉም ማለት ይቻላል።
ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ እነዚህ ነገሮች በጥቂት ሰዎች እጅ ወስጥ በመሆናቸው ነው። አውቀውትም ይሁን ሳያውቁት እነዚህ ሰዎች የፈጥራ ዘብ ሆነው ነገሮችን ይገድባሉ። እንዲህ ያለ ስልጣን በጥቂት ሰዎች እጅ ውስጥ ብቻ ሊኖር አይገባም። ወደ የተለመደ እና ተራ አሰራርን ያመራሉ። ይህ ደግሞ አደገኛ ነው። ምክንያቱም የራሱ ቀለም እና ብዝሃነት የሌለው ድምፅ ተፅኖዎች እንደ ፖለቲካ ፣ ትምህርት ፣ ሳይንስ እና እርሻ ያሉ ሌሎች ዘርፎችም ላይ ሊንፀባረቅ ይችላል። የቀሪው አለም ዋና ገበያ ገፅታም ቢሆን ያው ነው ፤ ጥቂቶች ላይ ብቻ ያተኮረ። በሩ ቢከፈትልን ፤ እኛ ግን ይበልጥ ጤናማ ፤ ባለብዙ ዘርፍ ፤ አካታች የሰራተኛ መደብ እና ለብዙዎች ባህል የቆምን ልንሆን እንችላለን።
ሌላው ነገር ደግሞ የባለሙያዎች እርዳታ ነው (ጠበቆች ፣ አካውንታንቶች ፣ ማኔጀሮች ፣ ህዝብ ግንኙነቶች ፣ የሙዚቃ ድግስ ለሙዚቀኛ ቦታ ያዦች ፣ የፈጠራ ሰዎች ፣ የድምፅ መሃንዲሶች ፣ ማስተሪንግ ፣ ሚክሲንግ ፣ አኪውስቲክ መሃንዲሶች ወዘተ…) የሉም እስኪያስብል ድረስ እጅግ ጥቂት ናቸው። ይህ ደሞ በራሳቸው ለሚሰሩ ሙዚቀኞች ሁኔታዎችን ማባሱ ጀብደኛ ከመሆን ይልቅ ግድብ እንዲሆኑ ያስገድዳቸዋል። የራሳቸውን መንገድ በመፈለግ ፋንታ አለም እና ሃገር ውስጥ ምን እየተሸጠ ነው ብለው ወጉን ይከተላሉ። ማነታቸውን ፤ ልዩ እና ብልህ የሚያደርግ አሻራቸውን አፍርሰው ተሰሚነትን ፤ ታዋቂነት እና ገንዘብ እናተርፍበታለን የሚሉትን መንገድ ይቀላቀላሉ።
ሙዚቃ እንደ ፊልምም ሆነ ሌሎች ዘርፎች የተለያየ ሙያ ያላቸው፤የተለያዩ ሰዎች እገዛ ስለሚያስፈልገው የራስህን ነገር ለመስራት የሌሎች ባለሙያዎች በቅርብ መኖር እጅግ አስፈላጊ ነው። ከማናጄሬ ጋር ብቻ አይደልም ተቀናጅቼ የምሰራው።
ከእኔ አልፎ ለሌሎች አርቲስቶችም ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር በማሰብ ዋግ(WAG) የተባለ የዝግጅት እና የውክልና ድርጅትን ፤ የፊልም ባለሙያ እና ማኔጀሬ ከሆነው ልዑል ሸዋፈራው ጋር አብሬ አቋቁሚያለው።

WHAT DO YOU THINK IS THE BEST WAY TO CULTIVATE A THRIVING MUSIC INDUSTRY?
People with means should invest in artists, not just musicians but writers, painters, filmmakers, and thinkers. People should encourage artists who take risks, who choose the untaken path; people should encourage everyone from Ethiopia, from every culture and region, to express themselves freely in the language they want to express themselves in, in whatever way they see fit.
Because without a diversity of artists, ideas, and thinkers, a society becomes like a plant that isn’t watered and given the right nutrients, and we all know what happens when you don’t water plants – they dry up and die. I mean that is the case worldwide too, tools for art creation and dissemination are in the hands of very few people, which also reflects into penury of imagination on the global mainstream music, film, and other art scenes, which in turn is a reflection of penury of ideas in the political, scientific and economic scene.
It is even more visible here because it is concentrated in even smaller amounts of people. To counter this, listeners should understand that listening is also an art and should diversify what they listen to, should support their local artists, be open-minded about what they listen to and artists should take risks even if it isn’t easy.
They should be bold and fearless because art is the research and development of life and if when we explore our entire cultural possibilities from not just Ethiopia but the continent and the world, when we let voices from the majority shine, diverse voices, diverse languages, ideas, and faiths – that is when we find solutions, that is when we find perspectives that are constructive, liberating and endless.

ስጋት ፣ ብዝሃነት እና ተስፋ
አቅሙ ያላቸው ሁሉ የፈጠራ ሰዎች ፤ ሙዚቀኞች ፣ ፀሃፊያን ፣ ሰአሊያን ፣ የፊልም ባለሙያዎች፣እና ባለሃሳቦች ላይ ኢንቬስት ከማድረግ ባለፈ አዲስ ነገር ለሞመከር የሚደፍሩትንም ማበረታታት አለባቸው።
ከየሁሉም የኢትዮጵያ ክፍልም ሆነ ባህል አዲስ መንገድ ለሚሞክሩ ሰዎች በራሳቸው ቋንቋ ፣ በነፃነት ራሳቸውን እንደልባቸው እንዲገልፁ እድሉን መስጠት ያስፈልጋል።
የጥበብ አይነቷ ካልበዛለት አንድ ህዝብ ተንከባካቢ እንዳጣ እና በደረቀ መሬት ላይ እንደበቀለ ዛፍ ነው የሚሆነው። የዛ አይነት ዛፍ መጨረሻ ደግሞ ምን እንደሚሆን መቼም ሁላችንም እናውቃለን። ይደርቃል፤ደርቆም ይሞታል። በአለማችንም ያለው ሁሌታ ይሄው ነው። የፈጠራ እና ማዋሃጃ መሳሪያዎች የሚገኙት በጥቂቶች እጅ ነው። የአለም ዋና የጥበብ ገብያም በሙዚቃው ፣ በፊልሙም ሆነ በሌሎች የፈጠራ ዘፎች ላይ ነፃ አስተሳሰብ እንደሚያስፈልገው ማሳያ ነው። ይሄም በተራው ፖለቲካው ፣ ሳይንሱ እና ኢኮኖሚው ላይ ይንፀባረቃል። እዚህ ደግሞ ከጥቂትም ጥቂት በሚባሉ ሰዎች እጅ ወስጥ መሆኑ ሁኔታው ጎልቶ እንዲታይ አድርጎታል።
የሙዚቃ አድማጮችም ፤ ሙዚቃ ማድመጥ በራሱ ጥበብ መሆኑን አውቀው ፤ ልክ እንደ ፈጠራው ዘርፍ እሱም ብዝሃነትን ይፈልጋልና ፤ የሚያደምጡትን የሙዚቃ አይነት ሳይገድቡ አዲስ ነገር በሞከር ሙዚቀኞቹን ሊያግዙ ይገባል። ጥበብ የህይወት ፍለጋ እና መዳበር ነውና ፤ ሳንፈራ ከኢትዮጵያ አልፈን የአጉራችንንም ሆነ የአለምን ባህሎች ስንዳስስ ለብዙሃኑ ድምፅ እንሆናልን። ብዙ አይነት ድምፆች ፣ ብዙ አይነት ቋንቋዎች ፣ ሃሳቦች እና እምነቶች! ያኔ ነው መፍትሄ የሚኖረው ፤ ያኔ ነው ገንቢ፣ነፃ አውጪ እና ማለቂያ የሌለው እይታ የሚኖረን!

MUSIC RECOMMENDATION
It’s not easy to recommend music because there are so many amazing musicians out there, but here are a few.
ሙዚቃ ቅጂ
መቼም ይሄ ሁላ ድንቅ ሙዚቀኞች ባሉበት ሙዚቃ መጋበዝ አስቸጋሪ ቢሆንም ጥቂቶችን እነሆ፡
CONTACT
YouTube @Ethiopian Records የኢትዮጵያ ልጅ
Facebook @Ethiopian Records. የኢትዮጵያ ልጅ
Instagram @ethiopian_records
Soundcloud @ethiopianrecords
መገኛ
ዮትዩብ @Ethiopian Records የኢትዮጵያ ልጅ
ፌስቡክ @Ethiopian Records. የኢትዮጵያ ልጅ
ኢንስታግራም @ethiopian_records
ሳውንድክላውድ @ethiopianrecords