PARC
Part of what makes the local music industry challenging is the lack of spaces where artists can fully commit to their art. If there are spaces available, are they accessible and affordable?
This is what Ezana Gettu wanted to address when he started the Performance Arts Resource Center (PARC) five years ago after immigrating back to Ethiopia from the United States. PARC was envisioned as a studio space where the artist can explore their art and work to become the best version of themselves. There aren’t many spaces like this.
We were curious to see what these spaces can do for up-and-coming musicians and sat down with Ezana to talk about his experiences in running PARC as well as his views on the Ethiopian music industry.
ፓርክ
የሀገራችንን የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ከሚያዳክሙ ነገሮች ውስጥ አንዱ አርቲስቶች ሙሉ ጊዜያቸውን ሰተው መስራት የሚችሉባቸው ቦታዎች እጥረት ነው። ቦታዎቹ ቢኖሩ ራሱ ተደራሽ እና ባለ ተመጣጣኛ ዋጋ ናቸው?
ኢዛና ጌቱ ይሄን ችግር ከግምት ወስጥ አስገብቶ ነበር ፤ የተከያኒ ጥበቦች ግብአት ማእከልን (PARC) ከአምስት አመት በፊት ከአሜሪካን ወደ ሃገሩ ተመልሶ የመሰረተው። ማእከሉ አርቲስቱ በነፃነት መስራት የሚችልበት ስቱዲዮ እንዲሆን እና ራሱን እስከመጨረሻው ማሳደግ የሚችልበትን መንገድ የማመቻቸት ራዕይ ይዞ ነበር የተቋቋመው። እንደሱ አይነት ቦታዎች ያን ያህል የሉም።
ቦታው በመምጣት ላይ ላሉ አሪስቶች ምን ያደርጋል ስለሚለው ፤ ፓርክን ከመሰረተ ወዲህ ስላለው ልምድ እና ስለኢንዱስትሪው ያለውን እቅድ ለማውራት ከኢዛና ጋር ቁጭ ብልን ነበር።
Why PARC?
Before coming here, the one thing people told me is there aren’t many places where an artist can be comfortable and just make music. It’s like what they say in Field of Dreams, you build it and they will come. It was that simple. I wanted to create a space where an artist can have an affordable alternative, where they can come and create music with no strings attached and no stress. We claim no ownership to a musician’s work. That’s not the standard here. Studios, not every studio, charge them a recording fee and on top of that a percentage from their work. Sometimes artists are forced to give up their work entirely. That’s insane!
It’s what I am trying to combat with PARC. Since there is no industry, it has become a free for all. I want to be the space that brings the best out of local artists. That’s crucial for an artist to actually make good music. There aren’t many spaces like this and by doing that you create a standard. Because certain key players in the industry are greedy here, they aren’t interested in shaping the industry but to get paid. Even though, in the long term, everyone can get paid with the proper infrastructure in place. There are over 100 million people here and you can have twenty record labels and everyone can be profitable but here we are.
ለምን ፓርክ?
ከመምጣቴ በፊት ብዙዎች አርቲስቱ በተረጋጋ መንፈስ ተመችቶት ሙዚቃ መስራት የሚችልበት ቦታ አለመኖሩን ይነግሩኝ ነበር። ፊልድ ኦፍ ድሪምስ ላይ እንደሚሉት አንተ ገንባው እንጂ ይመጣሉ። ቀላል ነበር። ለአርቲስቱ ኪስ ተስማሚ የሆነ እና ያለምንም ተያያዥ ጣጣ ሙዚቃ መስራት የሚችሉበትን ቦታ መፍጠር ነበር የፈለኩት። በስራቸው ላይ ምንም ባለቤትነት የለንም። እዚህ መመዘኛችን እሱ አይደለም። ስቱዲዮዎች ፤ ስቱዲዮ ብቻ አይደለም ፤ ለመስራት ካስከፈሉ በኋላ ከስራው ከሚያገኙት ገቢ ላይ በፐርሰት ይወስዳሉ። አንዳንዴ አርቲስቶ ስራውን ጭራሽ እርግፍ አድርገው ለመተው ይገደዳሉ። እሱ ደሞ እብደት ነው!
በፓርክ በኩል ለሱ ነው መፍትሄ ለማበጀት እየሞከርኩ ያለሁት። ኢንዱስትሪ ባለመኖሩ ምክንያት ለሁሉም ነፃ ነው። እኔ ደግሞ የሃገራችን አርቲስቶችን ተሰጥዋቸውን እስከመጨራሻ የሚያወጡበት ስፍራ መሆን ነው የምፈልገው። አርቲስቱ ጥሩ ሙዚቃ እንዲሰራ እሱ በጣም ወሳኝ ነገር ነው። እንደዚህ አይነት ቦታዎች ብዙ የሉም እንጂ ለገበያው ቋሚ መመዘኛ መፍጠር ይቻል ነበር። አንዳንድ የኢንዱስትሪው ቁልፍ ተጫዋቾች ስግብግብ ስለሆኑ ክፍያቸውን እንጂ ኢንዱስትሪውን መቅረፅ አያስጨንቃቸውም። ቢሆንም ግን ጊዜው ይረዘም እንጂ አስፈላጊው ሁኔታ ሲመቻች ሁሉም ተገቢውን ክፍያ መውሰዱ አይቀርም። መቶ ሚሊዮን ሰው ባለባት ሃገር ሃያ የሙዚቃ አሳታሚዎች ቢኖሩ ሁሉም የፍሬው ተካፋይ መሆን ይችል ነበር። ግን ይሄው እዚህ ነን።
What are your thoughts on the industry as a whole?
The way things are set-up here is a shame. It’s a free-for-all that abuses creators. It’s sad and wasteful of the talent. It’s hard to call it an industry. It’s nonexistent. It’s chaos. The industry doesn’t beget talent, people are ready to quit before reaching their peak. The key players that finance these creators are already profitable so they don’t see the point in changing things. It’s an “if-it’s-not-broken-don’t-fix-it” mentality.
Even with the internet, an equalizer for artists, they still find ways to abuse the artist. You have studios that produce music videos and it’s the best way for an artist to get out there but the way they designed the contracts and how artists enter leaves a lot to be desired. The musician still gets screwed. You have people making substantial profits over the works of the creators and not treating or paying them right.
It’s strange that people plaster their logos on an artists’ creation as if they themselves created it. The way things are done don’t even allow for the artist to pursue them legally. You hear of artists threatening these guys with physical violence and some do follow through. Question is, what did they have to do to the musician to get them to that level? It’s crazy. These players don’t think in the long term. The only way to compete with them and fight these systems is to treat the artist right and set a standard. Then when the artists join you, they’ll have no option but to follow suit.
Even if you think about the businesses that are supporting musicians, like beer companies, they have too much influence. They sponsor events and sort of start to place dominance over certain aspects of an artist’s music, event and brand. It’s unheard of in other countries. The audience should do that, not beer companies.
ስለ ኢንዱስትሪው በጠቅላላው ምን ታስባለህ?
እዚህ ያለው የነገሮች ሁኔታ አሳፋሪ ነው። የፈጠራ ሰዎችን መጠቀሚያ ለማድረግ ለሁሉም ክፍት ነው። አሳዛኝ እና ችሎታ የሚባክንበት ነው። ኢንዱስትሪ ነው ለማለት ይከብዳል። ኢንዱስትሪው የፈጠራ መወለጃ አይደለም። አለ ማለት አይቻልም። ድብልቅልቅ ያለ ነው። ቁልፍ ተጫዋቾቹ እንዳለ አትራፊ ስለሆኑ ነገሮችን የመቀየር ፍላጎት የላቸውም። “ካልተሰበረ አትጠግነው” አይነት አስተሳሰብ ነው ያላቸው።
ከኢንተርኔት እና ከአርቲስቶቹ ማስተካካያ ጋር እንኳን ፤ መጠቀሚያ ማድረጊያ መንገድ አያጡም። የሙዚቃ ቪዲዮ የሚሰሩ ስቱዲዮዎች ቢኖሩም እንኳን እና ለአርቲስቱ መታያ የሚሆንበት ትልቅ መንገድ ቢሆንም፤ውሎች የሚዘጋጁበት መንገድ እና አርቲስቶችሁ ወደ ውሉ የሚገቡበት መንገድ ብዙ የሚያስቀርባቸው ነው። ሙዚቀኛው አሁንም እንተጎዳ ነው። ከባለቤቱ በላይ አትራፊ የሆኑ እና የሚሆኑ እና ተገቢውን ክፋያ የማይሰጡ ብዙ ሰዎች አሉ።
እንደራሳቸው አርማቸውን የሰው ስራ ላይ ለጥፈው ሳይ ግራ ይገባኛል። ነገሮች የሚሰሩበት መንገድ አርቲስቱ በህግ ለመጠየቅ የሚችልበት እንኳን አይደለም። አርቲስቶች የአካላዊ ጥቃት ማስፈራሪያ ሲልኩ እና አንዳንዴም ሲያደርጉት ይታያል። ወደ እነሱ እንዲመጡ ሙዚቀኞች ምን ማድረግ ይችላሉ ነው ጥያቄው። እነዚህ ሰዎች ስለ ወደፊት አያስቡ። ከነሱ ጋር ለመወዳደር እና እንዲህ ያለን ስርአት ለመታገል ብቸኛው አማራጭ አርቲስቱን በትክክል በማስተናገድ ስራአት ማበጀት ነው።
The artists on the other hand, have this “talent is all I need” mentality that limits them. You have artists that place too much importance on that and limit the role of hard work in all this. In the States, you have to pay to perform on stage. It’s not easy. It’s not given to you. You’ve got to work on yourself. It’s not just about talent. There are a lot of people that can sing or make music. It’s about what you’re willing to do to get to the next level and put out original, authentic and quality music.
The good side of all this is that whoever sets the standards makes the new rules. This way of operation can’t last, it’ll fail and if you set the standard by partnering with great artists and gain the following with quality music, they will have no other options. What else are they going to do? Stop existing? Nope. To survive they’ll have to course correct and treat the creators better. Because the major standard is that low. Add the fact that there are no gatekeepers, there is no top guy, that in itself gives anyone that’s committed and willing to do the hard work a chance to make it. There’s no one holding you back in the strictest of sense of the word. Another bonus: the same people that are abusing their power don’t want to work, they make their money easy and that makes it easier for organizations like PARC to change things for the better.
The advent of the internet is also a beautiful opportunity for musicians and everyone else, even though it is being abused again by people that have the power. I wouldn’t be doing this without the internet. It’s an equalizer that helps people get out there and gain the necessary momentum to get their music heard. You see young artists are beginning to notice things and fight this system. I can only imagine what these artists and managers can do if they unify.
These communities are forming but it needs a leadership that makes the necessary sacrifices, that protects the creators and people that are doing right by the artist. It needs people that understand the importance of shaping an industry. That’s what we’re trying to do with PARC but it’s hard work.
እንደ ቢራ ፋብሪካዎች ያሉ አርቲስቱን የሚደግፉ ዘርፎችን ብንመለከት ራሱ ብዙ ተእፅኖ ያሳድሩበታል። የሙዚቃ ድግሶችን ስፖንሰር ካደርጉ በኋላ የአርቲስቱን እና ስራ ፣ ብራንድ እና የሙዚቃ ድግስ ላይ እንደ ባለቤት መሆን ይጀምራሉ። በሌሎች ሃገሮች ተሰምቶ የማያውቅ ነው ይሄ። አድማጩ እንጂ ቢራ አይደለም ይሄን ማድረግ ያለበት።
በሌላ በኩል ደግሞ አርቲስቱ “ችሎታዬ በቃኝ” የሚል አስተሳሰብ አለው። ሁሉ ነገሩን እሱ ላይ ብቻ በማደረግ እና የራሱን ሙዚቃ መስራት ላይ በመገደብ ይጠመዳል። አሜሪካን መድረክ ላይ ለማቅረብ መክፈል ይኖርብሃል። ቀላል አይደለም። ዝምብሎ የሚሰጥህ አይደለም። ራስህ ላይ መስራት ይኖርብሃል። ችሎታህ ብቻ በቂ አይደለም። ብዙ መዝፈንም ሆነ ሙዚቃ መስራት የሚችሉ ሰዎች አሉ። ነጥቡ ግን የራስህ የሆነ፤ኦሪጅናል እና ጥራት ያለው ሙዚቃ ለማቅረብ እና ወደሚቀጥለው ደራጃ ለመውጣት ምን ታደርጋለህ የሚለው ነው።
የዚህ መልካም ጎኑ ግን ስራቱን በስራው መቅረፅ የቻለ ነው ህጉን የሚያወጣው። ነገሮች የተቀመጡበት ሁኔታ ቋሚ አይሆንም። ስለዚህ ከስመጥር አርቲስቶች ጋር የሚወጣ ስርአት ከሆነ እና ጥራት ያለው ሙዚቃ ከተጨመረበት አማራጭ ያሳጣቸዋል። ምን ማደረግ ይችላሉ? መኖር ማቆም? አይ። ለመቀጠል ሲሉ አሰራራቸውን ማስተካለል እና አርቲስቱን በስርአቱ ማስተናገድ ይኖርባቸዋል። ምክንያቱም ዋናው መመዘኛ እንደዛ የወረደ ነው። ዘብ እና አንድ ጉልበተኛ ብቻ አለመኖሩ ጠንክሮ ከሰራ እና ፍላጎት ላለው ስኬታማ የመሆን እድሉን ይሰጠዋል። ወደኋላ ሊጎትትህ የሚችል ሰው አይኖርም። ሌላው ነገር እነዚሁ በአርቲስቱ ትከሻ የሚያተርፉ ሰዎች መስራት አይፈልጉም። ገንዘባችውን በቀላሉ ይሰራሉ። እሱ ደግሞ እንደ ፓርክ ላሉ ድርጅቶች ነገሮችን መለወጥ የሚችሉበትን መንገድ ያቀልላቸዋል።
የኢንተርኔት ሌላው መልካም ጎን ለአርቲስቱም ሆነ ለሁሉም ቆንጆ እድል መስጠቱ ነው። ምንም እንኳን በጉልብተኞች መጠምዘዙ ባይቀርም። ያለ ኢንተርኔት ይሄን ስራ መስራት አልችልም ነበር። ሙዚቃቸው እንዲወጣ እና ተደማጭነት እንዲኖራቸው የሚያመጣጥን ግፊት ይሰጣቸዋል። ወጣት አርቲስቶች ስርአቱን አስተወለው ለመታገል ሲሞክሩ እያየን ነው። እነዚህ አርቲስቶች እና ማኔጀሮቻቸው ህብረት ቢኖራቸው ሊሆን የሚችለውን ማሰብ ብቻ ነው የምችለው።
እነዚህ አካላት እየተከሰቱ ቢሆንም ተገሚውን መስዋትነት የሚከፍል ፤ ለፈጣሪዎቹ እና ለአርቲስቱ መልካም የሆኑትን አካልት የሚጠብቅ ጠንካራ አመራር ያስፈልጋቸዋል። ኢንዱስትሪውን መቅረፅ አስፈላጊ እንደሆነ የሚረዱ ሰዎች ሊኖሩት ይገባል። በፓርክ እሱን ነው ለማድረግ እየሞከርን ያለነው ፤ ከባድ ይሁን እንጂ።
What are performance spaces like here?
Since this is a free for all, the system sort of downplays the importance of musicians. Clubs tend to low-ball performers that can quite literally make or break a space. These spaces are important to these artists but they don’t understand the value of their music, especially up and comers. The other players see this as a carte-blanche to abuse. But what will happen if these performers decide not to show up? These clubs would lose their brand. We’ve seen it happen before and if things continue the way they are, it will happen again until they learn. It’s even crazier that these spaces use the same artists. If you go to Club A, you would hear the same sound as Club B, they are not allowed to actually perform new stuff. The owners of these spaces don’t understand the value of new sounds and how that can secure long-term profits.
These spaces are important to artists. They allow them to gain acceptance and a following locally. It’s everything to them and a space that sacred to them can’t be the space where they’re abused. Like I said before, the ones that have a chance now are the artists that perform cover songs of older hits. This is a young country where more than 40% of the population is under the age of 15 and 27% is around younger than 30. How long is that type of music going to last you?
እዚህ ይሉት መድረኮች ምን አይነት ናቸው?
ነፃ እንደመሆኑ ስርአቱ የሙዚቀኛው አስፈላጊነት ያቃልለዋል። ክለቦች ርካሽ ሙዚቀኞችን ይመርጣሉ፤ቦታውን ሊገነባው ሊያፈርሱት ቢችሉም እንኳን። እኒዚህ ቦታዎች አርቲስቱ አስፈላጊ ቢሆኑም እንኳን፤የሙዚቃቸውን ዋጋ አይረዱትም። በተለይም ጀማሪዎቹ። ለሎቹ አካላት ታድያ መጠቀሚያ ለማድረግ እንደ መልካም እድል ያዩታል። ግን እነዚህ አርቲስቶች ለመቅረት ቢወስኑስ? ክለቦችሁ ስማቸውን ማጣቸው አይደል?! ከዚህ በፊትም ሆኖ አይተነዋል። ስህተታቸውን እስካላልረሙ ድረስ መደገሙ አይቀርም። እነዛኑ አርቲስት ደግመው መጠቀማቸው ደግሞ ጭራሽ የሚገርም ነው። ክለብ ሀ የሰማኅውን ሙዚቃ ደግመህ ክለብ ለ ትሰማዋለህ። አዲስ ነገር እንዲጫወቱ አይፈቀድላቸውም። የነዚህ ቤት ባለቤቶች አዲስ ሙዚቃ የቋሚ ትርፍ ዋስትና መሆኑን አይረዱም።
በእርግጥ እነዚህ ቦታዎች አርቲስቶቹ የሃገር ውስጥ ተከታይ እንዲያፈሩ ይረዳቸዋል። እንደዛ የሚፈልጉት ቦታ ግን በስርአቱ የማይስተናገዱበት ሊሆን አይገባም። ቅድም እንዳልኩት ያላቸው አማራጭ ቆየት ያሉ ታዋቂ ዘፈኖችን አስመስለው መድገም ነው። ከ40% በላይ ህዝብ ከ15 አመት በታች እና 27% ከ30 አመት በታች የሆነባት ወጣት ሃገር ነው ያለችን። ታድያ እንደዛ አይነት ሙዚቃ እስከመቼ መቆየት ይችላል?
Where do you see the Ethiopian music industry going?
The hope I have for the music industry is the same I have for the country’s other industries. I want it to be the creative hub of Africa. We’re already the diplomatic hub. But in order for that to happen, we need to work together. I hope for people to wise up and learn that we need to stop working against each other.
This is an untouched place with potential. Ethiopia can be amazing. We are a country of 120 million people and they’re underserved. The local talent is waiting to be explored and be set free to create new sounds. The old ones are not going to last if we can’t invent. We need new sounds and we have the capacity to produce that. But it takes honest hard work and treating people right.
የኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ወዴት እያመራ ይመስልሃል?
ለሃገሬ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ የምመኘው ለሌሎች ኢንዱስትሪዎቿ ከምመኘው የተለየ አይደለም። የአፍሪካ የፈጠራ ማእከል እንድትሆን ነው የምፈልገው። አሁንም የዲፕሎማሲ ማእከል ነን። እሱ እንዲሆን ግን አብረን ልንሰራ ይገባል። ሰዎች ብልህ ሆነው እርስ በርስ ሳይሆን አብረን መስራት እንዳለብን ይረዳሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለው። ብዙ አቅም ያለው ያልተነካ ቦታ ነው። ኢትዮጵያ አስደናቂ መሆን ትችላለች። 120 ሚሊዮን ሰዎች የሚገባቸውን ያለገኙባት ሃገር ናት። ሃገር በቀል ችሎታ ገና ነፃ ሆኖ ለመስራት የሚጠብቅባት ናት። አዲስ ነገር ካልሰራን የድሮወቹ ብዙ አይቆዩም። ነገር ግን ታማኝ መሆን እና ሰዎችን በትክክል ማሰተናገደን ይጠይቃል።
Contact
Facebook @ThePARCEthiopia
Instagram @thep.a.r.c
YouTube @The PARC Studio
መገኛ
ፌስቡክ @ThePARCEthiopia
ኢንስታግራም @thep.a.r.c
ዮትዩብ @The PARC Studio