We live in a fast-paced and ever-changing world, where the advent of the internet is opening doors and opportunities for people from all walks of life. Technology has also pushed a great many things that were once considered essential or part of daily life into obsolescence, while calling into question the practicality of a great many more.
It’s a new age for those looking to make a name for themselves in the arts: resources exist in abundance at our fingertips; young creatives with unique voices are emerging, and audiences much more accepting than ever before. At such a convenient time, what makes spending years in music school worth it for artists determined to pursue music as a career path when they can simply learn on the job or simply from internet?
Girum Mezmur has been making his living as a musician for decades. A teacher at Jazzamba Music School, Girum is a firsthand witness to how much technology and new innovations have transformed the musical education scene. Still, he remains an ardent advocate for formal schooling for young artists.
“Even though I started out self-taught, the formal training I received after that has helped me understand international materials on jazz more easily” says Girum.
There are merits to his argument. Formal music education provides a detailed framework on music theory through structures that have been tried and tested over time; making the aspiring musicians literate in the language of music. With the ability to read notes, understand rhythmic patterns, construct interesting melodic phrasings and convey these ideas to other musicians, it exposes students to the general implications and cultural basis of music.
On the other hand, musicians who have pursued careers with no formal education argue that music is a language that can be self-taught and learned through collaboration with other artists.
“Even though I don’t believe everyone has to go through formal training to make it in the industry, a proper education with enough resources helps the artist in developing a discipline and understanding the cultural aspect of music,” says a self-taught artist who requested anonymity.
የምንኖረው በፍጥነት በመቀየር ላይ ባለች አለም ውስጥ ነው። የምንወደው ነገር ላይ ያደረሰን መንገድ ከእኛ በቀደሙ ብዙዎች የተጠረገ ነው። እጃችን ላይ አማራጮች እንደልብ አሉን። የተለየ ድምፅ ያላቸው ወጣት የፈጠራ ሰዎች ብቅ እያሉ ነው። እኛም ከሌላው ጊዜ በእጅጉ ለእዲስ ነገ ክፍት የሆን አድማጮች ሆነናል። እንደዚህ በተመቻቸ ጊዜ ታድያ አርቲስቱ በቀላሉ እየሰራ ከኢንተርኔት መማር እየቻለ ለምን ሙዚቃ ትምህት ቤት ይሄዳል?
ለተወሰኑ አመታት በስራአት ከመማር እና ራስን ከማስተማር መምረጥ በመምጣት ላይ ላሉ አርቲስቶች አሻሚ ጥያቄ ሆኖ ቆይቷል። የክፍል ውስጥ ትምህርት በተደጋጋሚ ተሞክረው የተረጋገጡ የሙዚቃ ንድፍ እና ፅንሰ ሃሳቦችን መስመር ባለው መንገድ ያስተምራል። እሱም ጀማሪውን አርቲስት የተማረ እና የሙዚቃ ቋንቋ አዋቂ ያደርገዋል። ኖታ ማንበብ መቻሉ፤የዜማ አጣጣልን መረዳቱ፤ውብ የዜማ ሃረግ መመስረቱ እናም እነዚህን ሁሉ ለሌች ሙዚቀኞች በቀላሉ ማስረዳት መቻሉ፤አርቲስቱ ከሙዚቃው ባህል አንፃር መስረት እንዲኖረው ያደርገዋል።
“ምንም እንኳን ራሴን በማስተማር ብጀምርም፤ከዛ በኋላ በክፍል ወስጥ መማሬ እንደ ጃዝ ያሉ አለም አቀፍ ድምፆችን እንድረዳ ረድቶኛል” ይላል ግሩም መዝሙር።
በሌላ በኩል ራሳቸውን ያስተማሩ አርቲስቶች፤የሙዚቃ ቋንቋን በጊዜ ሂደት እና ከሌሎች ባልሙያወች ጋር በመሆን የመሞከር ነፃነት ታክሎበት ራስን ማስተማር ይቻላል ሲሉ መከራከሪያ ነጥብ ያነሳሉ።የሙዚቃ ትምህርት ውድ እንደመሆኑ ትምህር ቤቶችም ተማሪው ትክክለኛውን እውቀት እንዲያገኝ አስፈላጊ የሆኑ ጥራት ያላቸው መሳሪያዎች የሏቸውም። የሙዚቃ ትምህርት በዩኒቨርስቲ ደረጃ ብቻ ነው የሚሰጠው። ከዛም ውጭ፤ከአርቲስት ቤተሰብ ከተወለዱ ወይም በቤተክርስቲያን ውስጥ ካደጉት በቀር ‘ሀ’ ብለው ለሚጀምሩ ሌሎች ብዙ አማራጭ የለም። ይህ ደግሞ ያለ በቂ ግብዓት በራሱ ለአመታት ሲማር ለቆየው አርቲስት፤ከልጅነታቸው ሙዚቃ እየተጫወቱ ከሚያድጉበት የምእራቡ አለም ሙዚቀኞች ጋር መወዳደርን የማይታሰብ ያደርግበታል።
“ምንም እንኳና በኢንዱስትሪው ውስጥ ስኬታማ ለመሆን ሁሉም ሰው የግድ ትምህርት ቤት መግባት አለበት ብዬ ባላምንም ፤ በበቂ ግባቶች የታገዘ እና ስርአት ያለው ትምህርት አርቲስቱ ስነምግባር እንዲያዳብር፣ባህላዊ ጎኑን እና ካንዱ ወደሌላው ትውልድ የሚተላልፈውን ጥበብ እንዲረዳ ያግዘዋል። ፔንታቶኒክ መሰርት ያደረጉ ድምፆች እንዳለመለመዳቸው፤የኢትዮጵያ ሙዚቃ፤ከተለያዩ ድምፆቹ፣መሳሪያዎችሁ እንዲሁም ከባህሉ አይነት መብዛት የተነሳ ልዩ ድምፅ አለው። ይሄን ደግሞ በስርአቱ ሳይማሩት መወከል አስቸጋሪ ይሆናል።” ይላል ራሱን ያስተማሪ አርቲስት ሃሳቡን ሲያካፍለን።
But how does music education work, specifically in the Ethiopian context?
The roots of formal musical education in the country stretch back nearly a century, to the reign of Emperor Haile Selassie I. By the 1940s, music lessons had become a standard extracurricular activity in secondary schools across the country and the students were regularly taking part in shows and performances.
The Menelik II Secondary School March Band and the Haile Selassie I Day School in Addis Ababa; the Harar Medhanialem Secondary School and Harar Teacher Training School in Harerge Province; the Woyzero Sighen Secondary School in Wello Province; Ras Darge High School in Arussi Province; and the Atse Gelawdiwos Secondary School in Shewa Province were among the educational institutions offering musical training to their pupils.
In 1954, Yared Music & Theatrical School, formerly known as the National School of Music, launched as the first higher institution dedicated to musical education in Ethiopia. Established in the capital, Yared owes its existence largely to music teachers who were primarily involved in training young Ethiopians in military bands.
The school has left an indelible mark on Ethiopian music over the past six decades, countless young musicians have come through its doors and later made a name for themselves, both domestically and on international arts forums.
However, Yared and other schools in the country are not without their flaws. Because music programmes are expensive, schools aren’t equipped with the sufficient equipment and musical instruments necessary for students.
The lack of strong music programmes in schools below the university level is also a serious drawback as many pupils enroll with little to no practical experience with music, except those lucky enough to have families that accommodate for this. Others may also join a music school with some experience playing in religious settings, such as churches.
Nevertheless, the majority enrolls and begins learning from scratch, making the process challenging, especially when the schools do not provide the level of access and mentorship the students require to succeed.
Girum, who has attended music lessons at Yared, points out that there are a lot of administrative gaps at the school.
“The curriculum at Yared wasn’t tailored to just the music department. Because it’s under Addis Ababa University (AAU), there is a problem in policy and management,” he said. “Courses that were supposed to be five years were reduced to four. This is a disadvantage because most students come here without prior exposure to music. Because of this, many withdraw in the second or third year in frustration.”
Other factors affecting the system would be the deterioration of musical instruments from year to year, with the high cost of buying replacements meaning that there simply aren’t enough to go around.
“During my time, there were few Ethiopian musicians who were simultaneously talented in fixing damaged music instrument as well as in tuning pianos. Experts Bahiru Tedla, former Bodyguard Orchestra staff, worked for decades at Yared and was primarily responsible for repairing music instruments” Timkehet Teffera states in her paper; Ethiopian Popular Music History Part One.
የሙዚቃ ትምህርት በታሪክ እስከ ሃይለሥላሴ ዘመን ድረስ ወደ ኋላ ይሄዳል። በተለይም በ40ዎቹ መጨረሻ ሙዚቃ በተጨማሪነት ከትምህርት ስርአቱ ጋር ተካቶ ነበር። ዳግማዊ ሚኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፤ሃረር መምህራን ማሰልጠኛ፤ወሎ ያለው ወይዘሮ ስህን ሁለተኛ ደረጃ ፤ አሩሲ ያለው ራስ ዳርጌ ሁለተኛ ደረጃ እና ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ናዝሬት የነበረው አፄ ገላዊዲዮስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የስተካከለ የሙዚቃ ትምህርት ስርአት የነበራቸው ነበሩ። ነገርግን ከአቢዮቱ ወዲህ መንግስት የሙዚቃ ትምህርትን እንደቅንጦት መቁጠሩ የማሳደግ ተነሳሽነቱን ገድሎታል።
በፈረንጆቹ 1954 በወቅቱ ብሄራዊ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ይባል የነበረው ያሬድ የመጀመሪያው የከፍተኛ ትምህርት የሙዚቃ ትምህርት ቤት ሆኖ ተቋቁሟል። በአብዝሃኛው በወታደራዊ ባንዶች ቤት ውስጥ ወጣቶችን ያስተምሩ ለነበሩ የሙዚቃ መምህሮች የያሬድ መቋቋም ትልቅ የምስራች ነበር። ሃገሪቷ የሙዚቃው እድገት ላይ ተእፅኖ በሚያሳድር ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ውስጥ ከማለፏ አንፃር ያሬድ ማስተማር የሚችሉ እና በሃገር ውስጥም ሆነ በውጩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያው ለውጥ ላይ አስተዋፆ ያላቸው ወጣቶችን በማፍራት ትልቅ ሚናን ለማስመዝገብ ችሏል።
ያሬድ ትምህርቱን የተከታለው ግሩም በትምህርት ስራቱ ላይ ያለውን ክፍተት እንዲህ ሲል ይገልፀዋል “ያሬድ የነበረው ትምህር ስርአት የሙዚቃ ብቻ አልነበረም። በአ.አ.ዩ ስር ስለሆነ የፖሊስ እና የአስተዳደር ክፍተቶች አሉበት። አምስት አመት መሆን የነበረበት የትምህርት ዘምን ወደ አራት ተቀንሷል። አብዛኞቹ ተማሪዎች በቂ የሙዚቃ ትውውቅ ሳይኖራቸው ስለሚመጡ ጎጂ ያደርገዋል። በዚህም ምክንያት ተማሪዎቹ ሁለት እና ሶስተኛ አመት ላይ ተሰላችተው ያቋርጣሉ። ፖሊሲው ሊሻሻል ይገባል።”
የሙዚቃ መሳሪያዎች ማርጀት እና የመግዣ ምንጭ አለመኖሩ፤እንዲሁም የአዲሶቹ ዋጋ ውድ መሆን ሌሎች ጫና አሳዳሪ ገፅታዎቹ ናቸው። በዛ ላይም ተምረው የነበሩት ሙዚቀኞች ተቀጣሪ መሆን የአስተማሪዎች እጥረት ፈጥሯል። ይህ ደግሞ በአስተማሪዎችም ሆነ በተማሪዎች ዘንድ እርካታ እንዳይኖር አድርጎታል። በዚህ ምክንያት ሲመሰረት እንደ ራዕይ የነበረው ጥራት ያለው ትምህርትን መስጠት ሊሳካ አልቻለም። ከዚህም አንፃር ብዙ ሰዎች ተመዝግቦ ከመማር ይልቅ ከሌሎች አርቲስቶች እና እየሰሩ መማርን ይመርጣሉ።
“እኔ በነበርኩበት ጊዜ ፒያኖ መቃኘትም ሆነ የተበላሹ መሳሪዎችን መጠገንን የተካኑ ጥቂት አስተማሪዎች ነበሩ። የቀድሙ የክቡር ዘበኛ አባል የነበረው ብርሃኑ ተድላ የሙዚቃ መሳሪያን በመጠገን ያሬድ ለአስርት አመታት ሰርቷል።” ትላለች ጥምቀት ተፈራ ፤ በመመረቂያ ፅሁፏ ላይ።
Policies such as the one that dictates that only musicians with a formal education are eligible to work there as teachers narrows the talent pool considerable and causes a shortage of educators. The problems are a source of dissatisfaction for students and teachers alike.
However, Yared is not the only option out there for those looking to get their start in music. Private music schools, such as the Mekane Yesus Seminary and Jazzamba, have opened their doors to aspiring musicians over the past few decades.
Girum, who taught at the institutions for several years, says that the fact that there were no guitar lessons at Yared while he was a student there later encouraged him to form a refined curriculum for Jazzamba.
በኋላም የብዙ ሰው የሙዚቃ ፍላጎት እና ከሙዚቃ ጋር ያለው ትውውቅ ሲዳብር መካነእየሱስ ሴሚነሪ፤ጃዝ አንባ እና ሌሎች የግል ትምህር ቤቶች መቋቋም ጀምሩ። 2003 እስከ 2009 ያሬድ ያስተማረው ግሩም እሱ በነበረበት ጊዜ የጊታር ትምህር አለመኖሩ ጃዝ አንባን ለማቋቋም እንዳነሳሳው ይናገራል።
ምንም እንኳን የግል ትምህርት ቤቶች መስፋፋት መልካም ቢሆንም፤የግል እና የህዝብ ትምህርት ቤቶች ግን በስርአት የተነደፈ እና ከሃገራችን የሙዚቃ ታሪክ እንዲሁም አለምአቀፍ የሙዚቃ መርሆች ጋር የተጣጣመ የትምህርት ስርአት ካለመኖሩ ተጎጂ ሆነዋል። ከዚህም የተነሳ በመምጣት ላይ ያሉ ወጣት የተካኑ አርቲስቶች ከስራ መማርን እንደአማራጭ ያዩታል። ከሌሎች አርቲስቶ ጋር መስራትን፤ተቀባይ መሆንን፤ክፍት መድረኮች፤ለሌሎች አርቲስቶች መድረክ ከፋች መሆን ካልሆነም በፈለጉት ፍጥነት መማር የሚችሉባቸው እና ከፍተኛ ትምህርት ሳይኖራቸው እንደፍላጎታቸው መማር የሚችሉባቸውን የግል ትምህርት ቤቶች መግባትን ይመርጣሉ።
ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ፤አለማቀፍ ትኩረት የሚገያኙ አርቲስቶችን ለማፍራት በከፍተኛ ትምህርት ደረጃ ብቻ ሳይሆን ከልጅነታቸው ጀምሮ ለሙዚቃ ቅርብ እንዲሆኑ ማድረግ ያስፈልጋል። እሱ ከልጅነታቸው የትኛው የሙዚቃ አይነት ላይ ፍላጎት እንዳላቸው ማወቅ እንዲችሉ ስለሚረዳቸው እና ትምህርት ቤቶች ደግሞ ብዙ ሃገር በቀል የሙዚቃ አይነቶችን መዳሰስ ስለሚያስችላቸው፤ባለተሰጥኦ አርቲስቶችን አለም አቀፍ እውቅና እንዲያገኙ ማድረግ ያስችላቸዋል። ለወደፊት የሙዚቃ ትምህርት ቤቶችን በአርቲስቶች ዘንድ ተመራጭ ለማድረግ አወቃቀሩ ሊከለስ ይገባል። ባለሙያዎችም ዘመናዊ ስርአት መቅረፁ ላይ ሚና ሊኖራቸው ይገባል።