አብራከዳብራ = እርስ

Fouschow

Performance Documentation


እኔ እና ቤቴ ግጥም የህያው ምስክር እንደሆኑ እናምናለን: ምናባዊ መገልጥም እንደሆነ እናምናለን: ለአያቶቻችንም ከመለኮት ጋም የሚገናኙበት መሰላል -ለአባቶቻችን የአብዮት ሰይፈ የሚስሉበት ሞረድ.ለእኛ ፈልግ እንደሆነ እናምናለን: ካልተንዛዛ ለቅሶ ካልቆረፍደ ተረት ያልተዝረከረከ ፍልስፍና እንደሆነ እናምናለን: ለገጣሚ ብቻ የተሰጠ መክሊት እንደሆነ እናምናለን: ገጣሚው ያላረገዘውን የማያምጥ: ያላማጠውን የማይወልድ: ያልወለደውን የእኔ ነው ብሎ እንደማይጠራ እናምናለን: በጭብጨባ ብዛት የማይለመልም በእርግማን ብዛት የማይመነምን እንደሆኑ እናምናለን: ከሁሉም በላይ ከዘመዶቹ ከሰው ልጆች የሚያግደ ልባም እንደሆነ እናምናለን: ይሄንንም እመሰክራለው

About the contributor

I began my childhood as Fouschow in Addis Ababa Ethiopia Fouschow was my name but not only mine it was everyone’s name all the kids I grow up with we all called each other “Fouschow, Fouschow, Fouschow”. The word Fouschow has no dictionary meaning but it holds an entire philosophy I AM BECAUSE WE ARE.